አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ተቋማት ለገበታ ለትውልድ የሚያደርጉትን ድጋፍ አሁንም እንደቀጠሉ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተለያዩ ተቋማት አምስተኛ ዙር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቋል።
በዚህም ሬዳዋ ሞተርስ ኢንዱስትሪ 15 ሚሊየን ብር ለግሷል።
በተጨማሪም ካንትሪ ትሬዲንግ፣ ኢስተርን ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ ሁደየብ ጀኔራል ትሬዲንግ፣ ቢ ኤንድ ሲ አሉሙኒየም፣ አያት ሸር ኩባንያ፣ ይርጋ ሃይሌ እና ቤተሰቦቹ፣ ዲ ኤም ሲ ትሬዲንግ፣ ከርቻንሴ ትሬዲንግ፣ ኪም ክዋንዎ፣ በያን ኢብሮ አብደላ፣ አኮርዲያ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ኑር ሱልጣን እና ቲ ኤን ቲ ኮንስትራክሽን ኤንድ ትሬዲንግ እያንዳንዳቸው 10 ሚሊየን ብር ለግሰዋል።
ጽህፈት ቤቱ ጥሪውን ተቀብለው ድጋፍ ላደረጉ ተቋማትም ምስጋናውን አቅርቧል።