አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በፈረንጆቹ 2024 ላይ በሚካሄደው ምርጫ በድጋሚ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ባይደን በዛሬው ዕለት በሠጡት መግለጫ ÷ “ለመወዳደር ዕቅድ አለኝ …ግን ከአስተዳደሬ ጋር ተማክረን ለአሜሪካ ሕዝብ በይፋ ለማስታወቅ ገና አልተዘጋጀንም” ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው በግልፅ ያስታወቁት በዛሬው ዕለት ከ“ቱደይ” ሾው ተባባሪ አዘጋጅ አል ሮከር ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልሥ ነው፡፡
የ80 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት ጆ ባይደን ባለፈው ዓመት በኋይት ሐውስ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አል ሻርፕተን ጋር በነበራቸው ቆይታም ለሁለተኛ ጊዜ የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን ኤን ቢሲ አስታውሶ ዘግቧል፡፡