አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታኒያ ፋየን ጋር ተወያዩ፡፡
ሚኒስትሯ በውይይታቸው መንግስት በመላ ሀገሪቱ በተለይም ግጭት በተከሰተባቸው የሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የወደሙ ጤና ጣቢያዎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ትኩረት ሰጥጦ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የስሎቬኒያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታኒያ ፋየን በበኩላቸው ÷ ሀገራቸው በጤናው ዘርፍ ውጤታማ ማሻሻያዎችን እያደረገች መሆኑን እና ኢትዮጵያ ከስሎቬኒያ ልምድ መውሰድ እንደምትችል ገልፀዋል፡፡
ስሎቪኒያ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ለመክፈት ማቀዷንም አስገንዝበዋል፡፡