አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰዎች ለሰዎች ድርጅት በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ ሳቢያ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች 100 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን የሰዎች ለሰዎች ድርጅት አመራሮች ለኦሮሚያ ክልል ገንዘብ ቢሮ ሃላፊ ቶሎሳ ጋዳፋ አስረክበዋል፡፡
ድጋፉ 2 ሺህ 510 ኩንታል የበቆሎ ዱቄት፣ 8 ሺህ 400 ሊትር ዘይት፣ 255 ኩንታል አተር፣ 265 ኩንታል አልሚ ምግብ እና ሌሎች ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡