የሀገር ውስጥ ዜና

የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

April 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሁለት ቀን ቆይታ ከመንግስት እና ከአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት አጋርነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ጣሊያን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሰብዓዊ እና የልማት ድጋፍ ማጠናከር ዋነኛ የቆይታቸው አጀንዳ ይሆናል ተብሏል።

ሀገራቱ በሚጋሯቸው ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!