የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

April 13, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሺ ዌንጁ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው አምባሳደር ተፈራ በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም እና በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ መክረዋል።

የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሺ ዌንጁ የቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ በአፍሪካ ኢንቨስት በማድረግ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ ረገድ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የቻይና ልማት ፈንድ በመጭው ሰኔ ወር በሚዘጋጀው የቻይና -አፍሪካ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየም ላይ አምባሳደር ተፈራን ጨምሮ የኤምባሲው ሰራተኞች እንዲሳተፉ ጋብዘዋል፡፡