አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚያዝያ 29 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2015ዓ.ም የሚካሄደውን11ኛው የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር ጉባዔን ሊያስተናግድ መሆኑን ገለፀ፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ በጉባዔው በርካታ ዓለም አቀፍ ኢንዱስትሪዎች ይሳተፋሉ፡፡
አጋጣሚው ለአየር መንገዱ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥርም ነው የገለጹት፡፡
በጉባዔው እስከ 500 ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አመላክተዋል፡፡
የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር ዋና ጸሐፊ አብዱራህማን መንቴ÷ በጉባዔው ላይ ስመጥር የአውሮፕላን አምራች ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ አንስተዋል፡፡
ይህም የአፍሪካ አየር መንገዶችን አቅም ለማሳደግ እንደሚረዳ ነው የተናገሩት፡፡
10ኛው የአፍሪካ አቪዬሽን የባለድርሻ አካላት ጉባኤ እ.አ.አ ግንቦት 2022 በኬንያ ናይሮቢ መካሄዱ የሚታወስ ነው።