የሀገር ውስጥ ዜና

የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል ተከበረ

By Mikias Ayele

April 14, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ተከበረ።

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፣ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት፥ በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎት እና በዝማሬ ነው የተከበረው፡፡

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚነበቡ ሲሆን፥ በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበም ይሰገዳል።