የሀገር ውስጥ ዜና

የፋሲካ እና የዒድ አልፈጥር በዓላትን አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ማክበር እንደሚገባ ተገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

April 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋሲካ እና የዒድ አልፈጥር በዓላትን አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ማክበር አለብን ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ገለጹ።

ከንቲባው መጪዎቹን በዓላት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም÷ የፋሲካ እና የዒድ አልፈጥር በዓላትን የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ እና የእርስ በእርስ አንድነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ማክበር ይገባል ብለዋል።

በዓላቱን የእርስ በእርስ ግንኙነትን በማጎልበት የሀገርን ታላቅነት ለማፅናት በአንድነት በመቆም ማክበር አለብን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዓላቱ የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆኑ ከንቲባው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!