የሀገር ውስጥ ዜና

የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ሌሊት 9 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል

By Amele Demsew

April 15, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ነገ የሚከበረውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ በመከላከያ ሚኒስቴር የስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የስነ ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ፖሊስ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው፥ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በዋዜማው ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ ይተኮሳል።

ህብረተሰቡም ተገቢው መረጃ እንዲኖረው አስታውቋል፡፡