የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ ሃላፊዎች ጋር ሲያደርግ የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ

By Mikias Ayele

April 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘባ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ሃላፊዎች ጋር ለአንድ ሳምንት ሲያደርግ የቆየውን ውይይት አጠናቅቋል፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሽ  በቀለ  (ዶ/ር)  በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት÷ በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተመራው ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ዳይሬክተሮች ጋር ሲያደርግ የነበረው ውይይት ተጠናቋል፡፡

የፋይናንስ ልዑኩ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አይ ኤም ኤፍ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ እና ልዑካቸው ጋር ምክክር ማድረጋቸውን እና ለአንድ ሳምንት የቆየውን ውይይት መጠናቀቁን አንስተዋል፡፡

የተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የልማትና ሰብዓዊ  ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡