አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክት ላይ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር እየመከረ ነው፡፡
በመድረኩ የኢትዮጵያ፣ የኬንያ እና የታንዛኒያ ተወካዮች እንዲሁም የዓለም ባንክ፣ የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽን እና ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጀክት አመራሮች ተገኝተዋል።
ወይይቱ በሃይል አቅርቦት፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በትራንስፖርት የስራ ዕድል ፈጠራ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ከሚተገብርባቸው የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የተሻለ አፈፃፀም አስመዝግባለች።
በፕሮጀክቱ ከሚደገፉ የልህቀት ማዕከላት የስልጠና መሠረተ ልማት ዝርጋታ ባሻገር ፕሮጀክቱ በክህሎት ልማትና ነፃ የጉልበት ዝውውር በማስፈን በቀጠናው ያሉ ሀገራትን ከማስተሳሰር አንፃር ሚናው ከፍተኛ ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!