የሀገር ውስጥ ዜና

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከትሬድ ማርክ አፍሪካ ጋር በጋራ ለመስራት ተስማሙ

By Amele Demsew

April 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከትሬድ ማርክ አፍሪካ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚነስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የትሬድማርክ አፍሪካ በኢትዮጵያ ዳይሬክተር እውነቱ ታዬ ናቸው።

ስምምነቱ የሀገሪቱን የጭነት ተሽከርካርዎች የገቢና ወጪ ሥራዎች ለማሳለጥ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ትሬድ ማርክ አፍሪካ የፋይናንስና ቴክኒካል ሥራዎችን የሚያከናውን ይሆናል፡፡

እንዲሁም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የክትትልና ማስተዳደር ተግባራትን እንደሚሰራ ነው የተገለጸው፡፡

ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ ስምምነቱ ኢትዮጵያ በሎጂስቲክ ዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን ያስችላል፡፡

አቶ እውነቱ ታየ በበኩላቸው÷ “ድርጅታችን የአፍሪካ ሀገራት የንግድ ትስስር ለማጠናከር በተለይም የነፃ ቀጣናዊ ንግድ ትስስርን ለማጎልበት ይሠራል ብለዋል፡፡

በታሪኩ ወ/ሰንበት እና አሸናፊ ሽብሩ