ስፓርት

በቦስተን ማራቶን አትሌት አማኔ በሪሶ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች

By Mikias Ayele

April 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ቦስተን ማራቶን አትሌት አማኔ በሪሶ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቃለች፡፡

አማኔ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ 50 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ሁለተኛ ደረጃን መያዝ የቻለችው፡፡

ርቀቱን ኬንያዊቷ አትሌት ሄለን ኦብሪ 2 ሰዓት ከ21 ደቂቃ 38 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት በበላይነት አጠናቅቃለች፡፡

በወንዶች የቦስተን ማራቶን ኬንያዊው ኢቫን ቼቤት ቀዳሚ ሲሆን÷ ታንዛኒያዊው አትሌት ጋብሬል ጌይ 2ኛ እንዲሁም ቤንሱን ኪፕሪቶ ከኬንያ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል በርቀቱ የተሳተፈው ሹራ ቂጣታ 14ኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቁን ከቦስተን ማራቶን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡