አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ) ጋር ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና ዩ ኤን ዲ ፒ በጋራ የሚያከናውኗቸውን ተግበራት በተመለከተ ግምገማ አካሂደዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ተቋማቱ የጋራ ጉዳዮቻቸውን አጠናክረው ለማስቀጠል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡