የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከ342 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By ዮሐንስ ደርበው

April 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ራዳ ክፍለ ከተማ ከ342 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በ90 ቀናት ተገንብተው የተጠናቀቁና የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ዛሬ ተመረቁ፡፡

በ90 ቀናት የተገነቡት ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችም ከ27 በላይ ሲሆኑ÷ ከ342 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸው ተገልጿል፡፡

ከፕሮጀክቶቹ መካከል÷ የህብረተሰቡን ኑሮ የሚያቃልል ዘመናዊ የዳቦ መጋገሪያ፣ የሸገር ዳቦና የአትክልት መሸጫ ሱቆች፣ የስፖርት ማዕከላት፣ የሕንጻ እድሳት እንዲሁም ግቢ ማሰዋብ እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል አፈጉባዔ ፋይዛ መሐመድ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻን ጨምሮ የከተማውና የክፍለ ከተማው አመራሮች ተገኝተዋል ።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!