የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ወጣቶች በመዲናዋ እየተገነቡ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

By Shambel Mihret

April 19, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ወጣቶች በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ከተጎበኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል በኮልፌ እየተገነባ የሚገኘው ኮልፌ ሪፈራል ሆስፒታል አንዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ወጣቶቹ የንፋስ ስልክ ሪፈራል ሆስፒታልን፣ የግብርና ምርት ገበያ ማዕከላት እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን እንደጎበኙ የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡