አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ግብይትን ከኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ውጪ በሚፈፅሙ የነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ገለጸ፡፡
ከሚያዚያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቢሮው አስታውቋል፡፡
ስለሆነም በአዲስ አበባ የሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች በሙሉ ከሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የነዳጅ ተጠቃሚዎችን በኤሌክትሮኒክስ ሥርዓት ብቻ ለማስተናገድ የቅድመዝግጅት ስራቸውን ከወዲሁ እንዲያጠናቅቁ ቢሮው አሳስቧል፡፡