የሀገር ውስጥ ዜና

በጅማ ዞን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

By Tibebu Kebede

April 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ባለሀብቶችና የተለያዩ ድርጅቶች ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፉ 18 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ፣ እህል እና የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና፣ ሳኒታይዘርና አልኮል ነው።

ከዚህ በተጨማሪም 4 ሚሊየን 500 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ፣ ሁለት ሆቴሎችን እና 5 ተሽከርካሪዎች ድጋፍ ማድረጋቸውን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሃኪም ሙሉ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ድጋፉ ለአቅመ ደካሞችና የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንደሚውልም ነው የተናገሩት።

ከድጋፍ ማሰባሰቡ ጎን ለጎንም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በዞኑ ባሉ ጤና ባለሙያዎችና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች የቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል።

እስካሁን ድረስ በዞኑ 21 ወረዳዎች ውስጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን፥ በጤና ተቋማት ውስጥ ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።

በሙክታር ጠሃ