የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለፊቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Melaku Gedif

April 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሲዳማ ሕዝብ ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው÷”እንኳን ለሲዳማ ሕዝብ ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አይዴ ጫምበላላ” ብለዋል።

የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ጉዱማሌ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል፡፡