አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ ጫምባላላ በዓል ደምቆ በተሳካ ሁኔታ ተከብሮ መጠናቀቁ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ዓለማየሁ ጢሞቲዮስ እንደገለጹት÷ በሐዋሳ ሲከበር የቆየው የፍቼ ጫምባላላ በዓል በሰላም ተጠናቋል።
በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ የመከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል።
የሲዳማ ሕዝብ እና የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡