አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ነገ ዓርብ (ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም) ከማለዳው 12:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዓሉ በሚከበርበት ሚያዝያ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ከማለዳው 12:00 ሰዓት ላይ በሚኒስቴሩ የሥነ-ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡
ዛሬ ማታ ጨረቃ በሳዑዲ ዓረቢያ በመታየቷ 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል ነገ በመላው ዓለም ይከበራል።