አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በተለያዩ ከተሞች በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ፡፡
በዓሉ በጅማ፣ሀረር፣በጅግጅጋ፣አሰላ፣በደብረብርሃን፣ አሶሳና በዲላ ከተሞች በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው የተከበረው፡፡
በከተሞቹ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች የሶላት ስነ-ስርዓትአካሂደዋል፡፡
በሙክታር ጠሃ፣ተሾመ ኃይሉና ኤልያስ ሹምዬ