አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በሚገኙ 153 ነዳጅ ማደያዎች የነዳጅ ሽያጭ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እየተከናወነ መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ነዳጅ ማደያዎች ባለሙያዎች እና የቴሌብር ወኪሎች ተሰማርተው አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
ደንበኞች ነዳጅ ለመቅዳት ሲሄዱ በቅድሚያ የቴሌብር አካውንት ከሌላቸው ቴሌብር ሱፐርአፕን http://xn--onelink-om4a.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል በቀላሉ ሂደቱን በመከተል እንዲመዘገቡ ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች፣ በአገልግሎት ማዕከሎች ወይም በቴሌብር ወኪሎች በኩል በቂ ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንት እንዲያስተላልፉ እና በየነዳጅ ማደያዎቹም በሚገኙ ወኪሎች በኩል ገንዘብ ገቢ በማድረግ የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ በቴሌብር መፈጸምም እንደሚችሉ የኢትዮ ቴሌኮም መረጃ ያመላክታል።