አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 33 ሚሊየን ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉ ከትምህርት ማህበረሰቡ የተሰበሰበ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
አልባሳትን ጨምሮ ምግብ እና የእንስሳት መኖን ያካተተ ድጋፍ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጎኖፋ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኤልዳና ሱሌማን በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!