የሀገር ውስጥ ዜና

ለአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ አስከሬን አቀባበል ተደረገለት

By ዮሐንስ ደርበው

April 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአንጋፋው አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ አስከሬን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ተደርጎለታል።

አቀባበሉን ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ናቸው፡፡

አርቲስት ዘሪሁን በሕንድ ሕክምና ላይ እያለ ባሳለፍነው እሁድ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱም ነገ ረቡዕ ሚያዝያ 18 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚፈፀም የቀብር አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታውቋል። #Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!