ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሱዳን ሃይሎች የ72 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ

By Melaku Gedif

April 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች የ72 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን÷ የተኩስ አቁም ስምምነቱ ከትናንት ሰኞ ዕለት አጋማሽ ሌሊት  ጀምሮ የሚተገበር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ በሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች መካከል 48 ሰዓታት የፈጀ ድርድር ከተደረገ በኋላ የተደረሰ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች ግጭት ውስጥ ከገቡ ወዲህ የተኩስ አቁም ስምምነትላይ ሲደርሱ ይህ ሶስተኛ ጊዜያቸው ነው፡፡የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች አሁን ላይ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ  የተለያዩ ሀገራት በሱዳን የሚገኙ ዲፕሎማቶቻቸውን ለማስወጣት ምቹ ሁኔታዎችን እንደሚፈጥር ተጠቁማል፡፡

11ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሱዳን ግጭት እስካሁን 427 የሚሆኑ ዜጎች ለህልፈት ሲዳረጉ÷ 3 ሺህ 700 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡