አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የዓመታዊው ዓለም አቀፍ የጉዞ ሽልማት (ወርልድ ትራቭል አዋርድ) በአራት ዘርፎች ዕጩ ሆኖ መቅረቡ ተገለጸ፡፡
ዓየር መንገዱ ÷ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገድ” ፣ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች የንግድ ምልክት”፣ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች ቢዝነስ ክላስ “ እና በ “ምርጥ የ2023 የአፍሪካ ዓየር መንገዶች ኢኮኖሚ ክላስ ” ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የሽልማት ዘርፎች ዕጩ መሆኑን የዓየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡
ዓየር መንገዱ ከታች በተቀመጡት ሊንኮች ድምፅዎን እንዲሰጡትም ጠይቋል