አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በካናዳ መሳሪያ በታጠቀ ሰው በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ኖቫ ስኮቲያ በተባለው አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት ሴት የፖሊስ አባልን ጨምሮ የ16 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
የአሁኑ ጥቃት ከ30 ዓመታት በኋላ በሃገሪቱ የተፈጸመ አስከፊው ጥቃት ነው ተብሏል።
ታጣቂው በተለያዩ አካባቢዎች የፖሊስ አይነት ተሽከርካሪን በመጠቀም ድርጊቱን መፈፀሙ ታውቋል።
ረዘም ላለ ጊዜ ከተደረገ የተኩስ ልውውጥ በኋላም ተገድሏል ነው የተባለው።
የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ሁኔታውን አሰቃቂ ብለውታል።
ወንጀለኛው ድርጊቱን ለምን እንደፈፀመ በመጣራት ላይ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ምንጭ፦ ሲ ጂ ቲ ኤን