የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ ልዑክ በትግራይ ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት የተጎዱ ፋብሪካዎችን ጎበኘ

By Meseret Awoke

April 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራው የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል ውቅሮ ከተማ በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን ፋብሪካዎችን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ የአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችና የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የልዑክ ቡድኑ በጉብኝቱ ሰማያታ የእምነበረድ ፋብሪካ እና ሸባ የቆዳ ፋብሪካን ተመልክተዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገለጻ ተደርጎላቸዋል።

ፋብሪካዎቹ በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው በፋብሪካዎቹ ይሰሩ የነበሩ በርካታ ዜጎች ለችግር መጋለጣቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮች በበኩላቸው ተቋማቱን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ መናገራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባሳለፍነው እሁድ ሰላምን ለማጽናትና ለትግራይ ክልል ህዝብ ያላቸውን አጋርነት በተግባር ለማረጋገጥ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በክልሉ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው ዛሬ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!