የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮ-ቻምበር ዓለም አቀፍ  ንግድ ትርዒት ተከፈተ

By Mikias Ayele

April 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 13ተኛው የኢትዮ -ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት በይፋ ተከፍቷል፡

የንግድ ትርዒቱን የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት፡፡

በዚህ የንግድ ትርዒት ላይ ከ250 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን እንደያቀርቡ ተመላክቷል፡፡

በዚህም መሰረት የተለያዩ አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን÷ የንግድ ትሪዒቱ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተጠቁሟል፡፡

በፍቅርተ ከበደ