የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረር የጅብ ትርኢት ማሳያ ፓርክ ግንባታ ተጀመረ

By Shambel Mihret

April 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመደመር ትውልድ መጻሕፍ ሽያጭ በተገኘ ገንዘብ በሐረር ከተማ የሚገነባው የጅብ ትርኢት ማሳያ ፓርክ የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ እና የግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ተካሄደ፡፡

የጅብ ምገባን ለሚመለከቱ ጎብኚዎች ሁኔታዎችን ምቹ በማድረግ ረገድ የማዕከሉ ግንባታ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ግንባታውን ያስጀመሩት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ÷ ግንባታው ያረፈበት ሥፍራና ዲዛይኑ ለጎብኚዎች እንዲመች ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

የመደመር ትውልድ መጻሕፍ ሽያጭም ከግንባታ ሥራው ጎን ለጎን መካሄዱን እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡

ከመጻሕፉ ሽያጭ በተጨማሪም የከተማዋ ማሕበረሰብ ለዚህ ዓለማ መሳካት ድጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

የሐረር ከተማን የቱሪዝም እና የልማት እንቅስቃሴ በማሳደግ ረገድ ፓርኩ የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ነው የተመለከተው፡፡

በመራኦል ከድር

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!