የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

By Shambel Mihret

April 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በአማራ ክልል ብልፅግና ፅህፈት ቤት ኃላፊ ግድያ የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ።

ርእሰ መስተዳድሩ ፥ የትኛውም የፖለቲካ ልዩነት በአፈሙዝ መፍታት ግዜ ያለፈበት ብቻ ሳይሆን ካለፍንባቸው የሩቅና የቅርብ ታሪኮቻችን መማር አለብን ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሀገራችን የአመለካከት ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድና በወይይት እንጂ በመሳሪያ አፈሙዝ መፍታትን የምትሸከምበት ጫንቃ የላትም ብለዋል።

ለሟች ቤተሰቦች፣ ለመላው የአማራ ክልል ህዝብ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን የተመኙት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ አሁን መላው ህዝብ ይህን ግድያ መቃወምና በቃ ሊባል ይገባል ማለታቸውን ከክልሉ መንገስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።