አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓየር ንብረት ለውጥ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እና ዘላቂ ምጣኔ ሐብት ለማረጋገጥ 18 ቢሊየን ዩሮ ተመደበ፡፡
ገንዘቡን የመደቡት የአውሮፓ ኮሚሽን እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ናቸው፡፡
በጀቱ ለአውሮፓ አጋር ሀገራት ንፁሕ የኃይል አቅርቦት አማራጮችን ለማዳረስ ብሎም የዓየር ንብረት ተፅዕኖን ለማቃላል ይውላል መባሉን የሕብረቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
በተጨማሪም በርሃማነትን ለመከላከል እንደሚውል ነው የተመለከተው፡፡