የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከ200 በላይ የከተማ ከንቲባዎች ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

April 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከመላው ኢትዮጵያ ለመጡ ከ200 በላይ የከተማ ከንቲባዎች ገለጻ አድርገዋል።

በመድረኩ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች መገኘታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

የውይይ መድረኩ የበለፀጉ ከተሞችን ለመፍጠር ከንቲባዎች በሚጫወቱት ሚና ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል፡፡