የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሽመልስ ከኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቯር ልዑካን ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

April 30, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተደዳድር ሽመልስ አብዲሳ ከኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቯር የልዑካን ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አቶ ሽመልስ በኦሮሚያ ክልል በግብርና ስራዎች የተከናወኑ ውጤታማ ተሞክሮዎችን ለልዑካኑ አብራርተዋል፡፡

ልዑካኑ በቀጣይ ቀናት በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተሰሩ የግብርና ስራዎችን እንደሚጎበኙም ከርዕሰ መስተዳድሩ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቩዋር ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለመጎብኘት ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡