አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመደመር ትውልድ መጻሕፍን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር÷ “የመደመር ትውልድ” መፅሐፍ ÷ አንድነትን፣ የዴሞክራሲ ሥርዓትን እና ተሥፋን በትውልድ ውስጥ ለማዳበር መሠረታዊ ሚና የሚጫወት መሆኑን ተናገረዋል፡፡
መጻሕፉ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚሸጥም ከወዲሁ የተጠበቀ ሲሆን÷ መፅሐፉን የማስተዋወቅ ሥራ ለአንድ ሳምንት እንደሚቀጥልም ነው የተገለፀው፡፡
ከመፅሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ዘመናዊ ቤተ-መጻሕፍት እና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች የሚገነቡበት መሆኑንም ገለጸዋል።
በትውውቅ መድረኩ የድሬዳዋ ባለሐብቶች ፣ ነጋዴዎች ፣ የካቢኔ አባላት እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች በመርሐ-ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!