የሀገር ውስጥ ዜና

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በክልሉ መልሶ ግንባታ ዕቅድ ላይ መከረ

By Amele Demsew

May 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

ካቢኔው በስብሰባው የክልሉን መልሶ ግንባታ አስመልክቶ የተዘጋጀ ዕቅድ ላይ መምከሩን የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ባለፈም በክልሉ በቀጣይ ወራቶች በሚከናዎኑ ተግባራት ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡ ነው የተገለጸው፡፡

የክልሉ ካቢኔ በመደበኛ ስብሰባው ወቅታዊ ሁኔታን በዝርዝር በመገምገም አቅጣጫ ማስቀመጡም ተጠቁሟል፡፡