የሀገር ውስጥ ዜና

የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የባለድርሻ አካላት ምክክር እየተካሄደ ነው

By Feven Bishaw

May 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በሐዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የመድረኩ ዓላማ በፓርኩ ያለውን ዕድል ለማሳየትና ባለሀብቶች መዋዕለነዋያቸውን እንዲያፈሱ ለማነቃቃት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት ግብርናን ለማዘመንና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ለማምጣት ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ለአንድ ቀን በሚቆየው መድረክ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሀመድ፣ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንታዬ ከበደ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ባለሀብቶች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ተወካዮች፣ የግል ባንኮችን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላትም በመድረኩ ተሳታፊ ናቸው፡፡