የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉን ወደ ሥራ የማስገባት ሥራ ሊጀመር ነው

By Mikias Ayele

May 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉን ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት ላይ ምክክር አደረገ፡፡

የትግራይ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ከላሌ አድሃና (ዶ/ር) ÷ ንብረቶች የወደሙና ሰራተኛውም ከስራ ገበታው ተለይቶ በመቆየቱ ከፍተኛ እገዛ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለዚህም አመራሮቹ ተቀራርበን ከተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር ዘርፉ ቀደም ሲል ወደ ነበርንበት ለመመለስ እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የደረሰውን ችግር ለመፍታት ድጋፍ እናደርጋለን ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ የሚገኘውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የደረሰበትን ጉዳት በአንድ ጊዜ ወደነበረበት ለመመለስ ባይቻልም ቅድሚያ ሰራተኛውን ወደስራ እንዲመለስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መሰራት እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡

ለዚህም በቅርቡ አንድ ልዑክ ወደ ትግራይ ክልል በመሄድ ጉብኝት እንደሚያደርግና ስልጠና እንደሚሰጥ ተጠቁማል፡፡