አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡
ጤና ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት አፈጻጸሙን ለቋሚ ኮሚቴው አቅርቧል፡፡
በዚሁ ወቅት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወርቅሰሙ ማሞ እንደገለጹት÷ በባለሙያ፣ በመድኃኒትና በደም እጥረት የሚሞቱ እናቶችን ቁጥር ለመቀነስ በትኩረት ሊሰራ ይገባል፡፡
ለእናቶች ሞት መነሻ ምክንያቶችን ለመቀነስም ጤና ሚኒስቴር፣ ተጠሪ ተቋማትና በየደረጃው ያሉ የጤና ባለሙያዎች ትኩረት እንዲሠጡ አስገንዝበዋል፡፡
መድኃኒት አቅራቢ ድርጅቶች የሚያሰራጯቸውን መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ለሚፈለገው አካ እና ዓላማ መዋላቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ከሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት የሚሠራው ሥራ አበረታች ስለሆነ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ተብሏል፡፡
የደም ዕጥረትን ለመፍታት በየሦስት ወሩ ከመደበኛ ደም ለጋሾች ደም የሚሰበስብበትን ስርዓት መዘርጋት ይገባል መባሉን የም/ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር)÷ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
መሠረተ ልማቶችን ለማስፋፋትና ግብዓቶችን ለማሟላት ሚኒስቴሩ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ባለሙያዎችን መድቦ በማሰራት ረገድም ሚኒስቴሩ ከጤና ቢሮዎች ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!