አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ያለንን የውሃና ሰፊ የመሬት ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ክልላዊ ኢኮኖሚን ማነቃቃት ይገባል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ተናገሩ፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ የዘጠኝ ወራት የግብርና ሥራዎች አፈጻጸም በሚዛን አማን እየተገመገመ ነው፡፡
ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በክልሉ የውሃና ሰፊ የመሬት አቅርቦት መኖሩ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ምቹ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ወቅቱን የጠበቀ ዝናብ መኖሩም ሌላኛው ለግብርና ልማት ስራ ምቹ ሁኔታ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
በቡና ልማት እና በአረንጓዴ ዐሻራ ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም መኖሩን ጠቁመው በቀጣይም ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡