የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች አቤቤ 13ኛውን የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት አውደ ርዕይ አስጀመሩ

By Mikias Ayele

May 04, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ሙያ እና ክህሎት ለስኬት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን 13ኛውን የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት አውደ ርዕይ አስጀመሩ፡፡

አውደ ርዕዩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የተዘጋጀ ነው።

በአውደ ርዕዩ የተለያዩ የምርት ውድድሮች እንደሚካሄዱና አሰልጣኞችና ተማሪዎች አዳዲስ የፈጠራ ውጤቶችን የሚያቀርቡበት መሆኑን ከከንቲባ ጽህፈት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።