የሀገር ውስጥ ዜና

ታዋቂው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

By Amele Demsew

May 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ታዋቂው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች ዳዊት ፍሬው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

በቅርቡ ለሥራ ወደ ጣሊያን ሀገር የተጓዘው ክላርኔት ተጫዋች ሙዚቀኛ ዳዊት ፍሬው በተኛበት ክፍል ሕይወቱ አልፎ መገኘቱን ከቅርብ ወዳጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡