ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ

By Alemayehu Geremew

May 08, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

ወላይታ ድቻና አዳማ ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

የአዳማ ከተማን ግብ ዮሴፍ ታረቀኝ 65ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር÷የወላይታ ድቻን ደግሞ ቢኒያም ፍቅሩ 82ኛው ላይ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደረጉት ፋሲል ከነማ እና አርባ ምንጭ ከተማ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የአርባ ምንጭ ከተማን ግብ ተመስገን ደረሰ ከእረፍት በፊት ሲያስቆጥር÷ የፋሲል ከነማን ደግሞ በዛብህ መለዮ በ78ኛው ደቂቃ ላይ አስቀጥሯል፡፡