የሀገር ውስጥ ዜና

የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ ታስቧል – ምርጫ ቦርድ

By Alemayehu Geremew

May 10, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 ዓ.ም የትግራይ ክልልን ጨምሮ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ምርጫ ለማካሄድ ማቀዱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።

ቦርዱ የ2015 በጀት ዓመት ያለፉትን 9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ማቅረቡን ኢቢሲ ዘግቧል።