የሀገር ውስጥ ዜና

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

May 10, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ከተለያዩ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ በብሪታኒያ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ጎን ለጎን ነው ከተለያዩ ሀገራት አቻወቻቸው ጋር የመከሩት፡፡

በውይይታቸውም÷  ኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ላይ እያደረገችው ያለውን ለውጥ እና ስራ አብራርተዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ አንደሆነ  መናገራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡