የሀገር ውስጥ ዜና

ብሔራዊ ባንክ፥ለሳፋሪኮም የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ሰጠ

By Melaku Gedif

May 11, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ ባንክ፥ ሳፋሪኮም የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት እንዲጀምር የሚያስችለውን ፈቃድ ሰጠ፡፡

የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ እንዳስታወቁት÷ ባንኩ የዲጅታል ፋይናንስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ለሳፋሪኮም ሰጥቷል፡፡

ይህም ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የሞባይል የገንዘብ ክፍያ አገልግሎት ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ኩባንያ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ባንኩ በጥሬ ገንዘብ የሚደረግን ግብይት በዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለመተካት የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፍም አረጋግጠዋል፡፡