የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ሲሚንቶ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወሰደ

By Shambel Mihret

May 11, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ያወጣውን የሲሚንቶ መሸጫ ዋጋ በመተላለፍ ከታሪፍ በላይ ሲሸጡ የተገኙ 89 የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው መንግሥት ያወጣው የሲሚንቶ ማከፋፈያና የችርቻሮ ተመን ዋጋ እንዲከበር ተደጋጋሚ ውይይት ማድረጉን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማና በለሚኩራ ክ/ከተማ ከተተመነው የሲሚንቶ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በላይ በመሸጥና ምርት በመደበቅ 58 ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል፡፡

በተመሳሳይ ከታሪፍ በላይ በመሸጥ 10 ሱቆች እና ምርት በማሸሽ 21 የመሸጫ ሱቆች ላይ እርምጃ መውሰድ መቻሉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቢሮው የተጀመረውን አሰራር የማስጠበቅ ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ያስታወቀው፡፡ላይ ንግግር  ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።