የሀገር ውስጥ ዜና

91 የምግብ ምርት ዓይነቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ታገዱ

By Meseret Awoke

May 11, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ይፋ መደረጋቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ።

እንደባለስልጣኑ መረጃ በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ሳያሟሉ ተመርተው እየቀረቡ ያሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል።

የተከለከሉትም በአጠቃላይ 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች መሆናቸውን አስታውቋል።

46 ዓይነት አይኦዳይዝድ ጨው፣ 27 ዓይነት የምግብ ዘይት፣ 10 ዓይነት ከረሜላ ፣5 ዓይነት አቼቶ 2 ዓይነት የለውዝ ቅቤ እና አንድ የቫኔላ ፍሌቨር ምርቶችን እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ምርቶቹ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የመጠቀሚያ ጊዜ፣ የአምራች ድርጅታቸው ስም፣ አስገዳጅ ደረጃ ምልክት፣ መለያ ቁጥርም ሆነ አድራሻቸው ምርቱ ላይ ያልተገለጸና የሌላቸው በመሆኑ የተነሳ ነዉ።

ምርቱ ሊይዛቸው የሚገቡ ንጥረ ነገሮች በውል ለማይታወቅ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ የሌላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

ለጥንቃቄ የምርቱ ዓይነትና የተገኙትን ክፍተቶች ይፋ በማድረግ ህብረተሰቡ በትኩረት ተመልክቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግም ጠይቋል። በዚህም የተከለከሉ የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች እና ብራንድ ስማቸው የሚከተሉት ናቸው ፡-

የምግብ ጨዉ

1. ሳባ የገበታ ጨው(Saba IODIZED Salt) 2. ንጋት የገበታ ጨው(Nigat IODIZED SALT) 3. አዲስ ብርሃን የገበታ ጨው ADDIS BERHAN IODIZED SALT 4. ሙና የገበታ ጨው(MUNA TABLE SALT) 5. ቤዝ የገበታ ጨው/BASE IODIZED SALT 6. ጉስቶ የገበታ ጨው/GUSTO IODIZED SALT 7. ማክ የገበታ ጨው/MAK IODIZED SALT 8. አባይ የገበታ ጨው/ABAY TABLE SALT 9. መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFINED & IODIZED SALT 10. መነስ ጨው /MENES IODIZED SALT 11. ሙሉ የገበታ ጨው /Mulu Table Salt 12. ኢርኮ አዮዳይዝድ ጨው ERKO IODIZED SALT 13. አርዲ የገበታ ጨው/ARDI IODIZED SALT 14. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT 15. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT 16. ጨረቃ የገበታ ጨው/IODIZED SALT 17. ፋና የገበታጨው/Fana Table Salt 18. ዳናት የገበታጨው 19. ሶም የገበታጨው/som iodized salt 20. ጉግሳ በአዮዲን የበለፀገ የገበታጨው/GUGSA Iodised Salt 21. ሸጋ ጨው/SHEGA Iodized SALT 22. ፍዳክ የገበታ ጨው/FDAK IODIZED SALT 23. ኡሚ የገበታ ጨው/UMI IODIZED SALT 24. ጊዜ አዮዳይዝድ ጨው/GIZE IODIZED SALT 25. ባማክ የገበታ ጨው/bamak Iodized Salt 26. ማዚ የገበታ ጨዉ/MAZI IODIZED SALT 27. አዲስ የገበታ ጨዉ/ADDIS Iodized Salt 28. የገበታ ጨው/Iodized salt 29. TANA TABLE SALT/ጣና የገበታ ጨው 30. ጣና የገበታ ጨው 31. ማኢዳ የገበታ ጨው/MAEEDA IODIZED SALT 32. አሚን ጨው/Amin iodized salt 33. ሆም የገበታ ጨው/HOME IODIZED SALT 34. ጂኤም የገበታ ጨው/GM IODIZED SALT 35. ገዳ አዮዳይዝድ የታጠበ የገበታ ጨው/ GEDA IODIZED SALT 36. ዛማ አዮዳይዝድ የታጠበ ባለ አዮዲን ጨው /ZAMA SALT 37. ሶሲ የአዮዲን ጨው/Sosi Iodized Salt 38. ብቁ የገበታ ጨው/Biku iodized salt 39. H.T.F TABLE SALT /ኤች.ቲ.ኤፍ 40. AFRAN Iodized Salt 41. ኤምሬት ጨው/Emirate IODIZED SALT 42. ስፔሻል የገበታ ጨው/Special Iodized Salt 43. ሊያ የገበታ ጨው/ LIYA IODIZED SALT 44. አፊ ጨው/AFI IODIZED SALT 45. ዩስራ ጨው/ YUSERA SALT 46. ቡዜ የገበታጨው/BUZE IODIZED SALT

የምግብ ዘይት

1. ነጃ ንጹህ የምግብ ዘይት/ NEJA Pure Edible Oil 2. ረና ንጹህ የምግብ ዘይት/ Rina Edible Pure Food Oil 3. የኛ ንጹህ የምግብ ዘይት/Yegna Pure Edible Oil 4. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት /Nura Pure Edible oil 5. ሕይወት ንጹህ የምግብ ዘይት /HIWOT Edible Cooking Oil 6. ሚድ ንጹህ የምግብ ዘይት /MID Pure Edible Oil 7. ጉና ንጹህ የኑግ የምግብ ዘይት/GUNA Pure Niger Edible Oil 8. አዲስ ንጹህ የምግብ ዘይት 9. ኑር ንጹህ የምግብ ዘይት/Nur Pure Edible Oil 10. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት/NuraPure Edible Oil 11. ሶፊ ንጹህ የምግብ ዘይት/Sofi Pure Edible Oil 12. ደሴት ንጹህ የምግብ ዘይት/Deset Pure Food Oil 13. HADI COOKING OIL 14. Arif cooking oil 15. ሰነዓ ንፁህ የምግብ ዘይት /Senea pure food oil 16. ቃል ንፁህ የምግብ ዘይት/Kale Pure Food Oil 17. ናዲ የተጣራ ንጹህ የምግብ ዘይት/ Nadi pure food oil 18. ሰላም ንፁህ የምግብ ዘይት/Selam pure food oil 19. ኑኑ ንፁህ የምግብ ዘይት /Nunu pure food oil 20. MIFTAH pure food oil 21. ቤላ የተጣራ የኑግ ዘይት/BELLA Pure Niger Oil 22. ጣዝማ ንፁህ የምግብ ዘይት 23. ሚና ንፁህ የምግብ ዘይት 24. ብሌን ንፁህ የምግብ ዘይት/Blen Pure Edible Oil 25. ደስታ የተጣራ የኑግ ዘይት 26. ሐዲ የተጣራ የምግብ ዘይት 27. ሳራ የኑግ የምግብ ዘይት/Sara Niger Oil

የከረሚላ ምርቶች

1. ማሂ ከረሚላ/Mahi candy 2. ኢላላ ጣፋጭ ከረሚላ/Elaala sweet candy 3. ፋፊ ሎሊፖፐ/Fafi lolipop 4. ኢላላ ሎሊፖፕ ቢግ ጃር/Elaala lolypop big jar 5. ኮከብ ከረሚላ/KOKEB candy 6. ከረሚላ 7. ከረሚላ 8. ኤም ቲ ሎሊፖፕ/MT Loliipop 9. ኤ.ኤ ከረሚላ/A.A candy 10. ምንም ገለጭ ፁሑፍ የሌለው ከረሜላ

የአቼቶ ምርቶች

1. ሮያል አቼቶ/Royal VINEGAR 2. ዋልታ አቼቶ 3. ሮያል አቼቶ/ROYAL Vinegar 4. ሌመን አቼቶ/LEMEN ACETO 5. ሸገር አቼቶ/SHEGER ACETO

የለዉዝ ቅቤ

1. በእምነት ኦቾሎኒ ቅቤ/BEMNET PEANUT BUTTER 2. ናይስ/Nice peanut butter

የቫኔላ ፍሌቨር

1. ምንም ገላጭ ጽሑፍ የሌለው የቫኔላ ፍሌቨር